የቁም ደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
OFWE/BA06/2012
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ፣ በረክ፣ እንጦጦ የካ፣ ጅባት ጌዶ እና ምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሁለተኛ ጊዜ ያወጣ
በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ ምስራቅ ሸዋ፤ እንጦጦ የካ እና በረክ ዲስትሪክቶች ድስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:
- የጊንድላ ፤ የአጣና ፤ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /አይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታው የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ጨረታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጣበትን ቀን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ጨረታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡ የቁም ባህርዛፍ ደን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 6% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ:
በስልክ ቁጥር 011 124 02 49 መደወል ይችላሉ፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት