በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም ለመሰረተ ልማት ግንባታ የሚውሉ ማሽነሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሟሟላት ይኖርባችኋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT) እና TIN ተመዝጋቢየሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር በመክፈል ከሱሉልታ ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ዕቃ ግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- በ21ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታ ሰነዱን እስከ 4፡00 ሰዓት ገብቶ ወዲያው 4:30 የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም።
- ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሐምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት የማሽነሪ ኪራይ ዋጋ ነዳጅንና ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እየገለጽን ለበለጠ መረጃ
- በስልክ ቁጥር፡- 0111860368 በመደወል ወይም ሱሉልታ ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ዕቃ ግዥ ክፍል በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ፡፡
የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር
ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት