የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OFWE/GU06/2012
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋራ ሙለታ ዲስትሪክት ስር የሚገኙትን የቁም የፈረንጅ ጥድ የቁም ደኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሁስተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ጅማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስግሞ ሰጠማ ድስትሪክት እና ኢሉአባባራ ቅርንጫፍ ፅ/ ቤት ገባ ዲደሳ ድስትሪክት ስር የሚገኙትን የቁም የፈረንጅ ጥድ የቁም ደኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡
- የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TiN” number ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 100. 00 / መቶ ብር / በመክፈል ቀበና ሼል /ኦይል ለቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ሐረርጌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ ኢሉአባቦራ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት መቱ ከተማ እና ጅማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጅማ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ጨረታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ጨረታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት እና የሚዘጋበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- .ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና (Bidbond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላለ ዋጋ 6% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ /CPO/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ፡ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111240249 በመደወል ማጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት