የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 01/2013
በኢፌዴሪ. ገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል:
- ሠራተኞች የደንብ ልብስ
- የፅህፈት መሣሪያዎች
- የንፅህና መጠበቂያና የፅዳት ዕቃዎች
- የተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- በዘርፉ የተሰማሩበት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፤ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት (Tin No.) የሚያቀርብ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት በባንክ የክፍያ ማስያዣ (CPO) ወይም በጥሪ ገንዘብ በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ አሠርተው ማስያዝ የሚችል፡፡
- ተጫራቾችን የጨረታ ሰነዱን ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ11፡00 እና ቅዳሜ ከ2፡00 – 6.00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመንጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አዋሽ ባንክ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ግዥና ፋይናንስ ክፍል ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የዕቃዎችን ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ክፍል አራት ላይ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በመምታት ዋናውንና ኮፒውን በማሸግ በቅ/ጽ/ቤት ስም የጨረታ መለያ ቁጥርን በመግለፅ በፖስታ ላይ በመፃፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ሰዓት ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የጨረታ ሰነድ መቀየር፣ ማሻሻል ወይም ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- የተሰረዘ፣ የተደለዘ፣ የተፋፋቀ ወይም በግልፅ የማይነብብ የጨረታዕቃዎች ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- . ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047-211-23-33/ 09-23-0660-26/ 09 36-11-68-88 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት