ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር የው/ድ/ያው/
አገ/ድ/ማስ/ማዕከል ግዥ ዴስከ ግ/ጨረታ 01/2013
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ድጋፍና የውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ማሰልጠኛ ማዕከል በ2013 በጀት ዓመት ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚህ መሠረት፡-
- ሎት 1 ሎት የተለያዩ አልባሳት (ደንብ ልብስ)
- ሎት 2 የጽሕፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች
- ሎት 4 የኮንስትራክሽን መሣሪያ ዕቃዎች
- ሎት 5 የኦፊስ ማሽን ጥገና አገልግሎት
- ሎት 6 የመኪናና የጀነሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 7 የወተትና የፍራፍሬ ዱቄት
- ሎት 8 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 9 የስፖርት መሣሪያ ዕቃዎች
- ሎት 10 የጥበቃ አገልግሎት
- ሎት 11 ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ አገልግሎት
በዚህ መሠረት በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል።
- ጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ዓይነቶች (ዘርፎች) ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝግቦ /ከፋይነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕቃው ዓይነት ኤንቨሎፕ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመስስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ (አሪድ ካምፓስ) አለፍ ብሎ ወደ ኩሓ በሚወስደው አስፋልት መንገድ በስተግራ በኩል ያለው የው/ድ/የው/አገ/ድ/ማስ/ማዕከል ግዥ ዴስክ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በቀን ኅዳር 4/03/2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:30 ሰዓት በዕለቱ በመቀሌ የው/ድ/የው/አገ/ድ/ማሰ/ማዕከል አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ፡– በስልክ ቁጥር 0344-40-70-64 (0948559345) ይደውሉ
በኢ.ፌ.ዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር
በህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ
ድጋፍና የውጊያ አገልግሎት ድጋፍ
ማሰልጠኛ ማዕከል