የቢሮ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢፌዲሪ የግ/ድ/ሰ/ማ/ዋ/ኤጀንሲ የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ሊቢሮ መገልገያ የሚውል ህንጻ ወይም ቪላ ከታኅሣሥ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል
በዚሁ መሠረት፡-
- መ/ቤታችን ለቢሮ የሚፈልገውን ከፍሎች ብዛት እና ዝርዝር መስፈርት ያዘጋጀ ስለሆነ አከራይ የመስፈርቱን ሰነድ በነፃ ከጽ/ቤቱ ግዥ ከፍል በመውሰድ የወር ኪራይ ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው በ21ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ይታሸግና በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ 9፡00 ሰዓት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
- አከራይ ተጫራቾች የኪራይ ዋጋውን ሞልተው ሰነዱን በሚመልሰ በት ወቅት የይዞታ ሰነድ /ካርታ/ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
- ሪጅን ጽ/ቤቱ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
በኢፌዲሪ የግ/ድ/ሰ/ማ/ዋ/ ኤጀንሲ
የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት
ጂማ