ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ድጋሚ ጨረታ ቁጥር 01/2012
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል ለ2012 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ
- የስፖርት አልባሳት፣
- የስራ ቱታ፣
- ወታደራዊ ጫማ እና
- ስፖንጅ ፍራሾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ሰይመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ሕጋዊ የአቅራቢዎች ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜአቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡
- በገንዘብ ሚ/ር በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም 2012 ዓም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች ለተለያዩ የስፖርት አልባሳት፣ የስራ ቱታ፣ ወታደራዊ ጫማ እና የስፖንጅ ፍራሾች ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ስም ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ እቃዎች ናሙና በጨረታው መክፈቻ ዕለት የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድመቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የእንግዳ መቀበያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 3/2012 ዓ. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ዕቃውን እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስልክ ቁጥር 011-1-24-12-42
- ፋክስ ቁጥር 011-1-226292
- የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል የፋይናንስ
አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል