የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 07/2012
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል ለ2012 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የሠራዊቱ የነፍስ ወከፍ የደረት ትጥቅ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ሕጋዊ የአቅራቢዎች ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜአቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም።
- በገንዘብ ሚ/ር በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም 2012 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- እያንዳንዱ ተጫራች ለሠራዊቱ የደረት ትጥቅ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ስም ማቅረብ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የደረት ትጥቁን ናሙና የጨረታውን ሰነድ በሚገዛበት ጊዜ በመመልከት ናሙናዎቹን በጨረታው መክፈቻ ዕለት የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የእንግዳ መቀበያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 26/2012 ዓ. ከቀኑ 7፡00 ተዘግቶ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራች ትጥቆቹን እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011-1-24-12-42፤
ፋክስ ቁጥር 011-1-226292
የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል የፋይናንስ
አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል