የተለያዩ አገልግሎቶች እና የዕቃዎች ግዥ ጨረታ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃ እና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የሠራተኞች ሰርቪስ የሚሆን ተሽከርካሪ ሎት 1 ፣
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ጫማዎች ሎት 2፣
- የተለያዩ ዕቃዎችን ለማስቀመጫነት የሚያገለግል መጋዘን ሎት 3 እና
- ለመስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ለሆኑ ለሕፃናት ልጆች ማቆያ (ዲኬር) ሎት 4
በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ
- የአቅራቢነት ማስረጃ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው
- የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ የሚችል ሲሆን የጨረታው ሰነድ የሚገኝበት ቦታ– ጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት አድራሻ ኢኮኖሚክስ ኤንድ ቢዝነስ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የሚገኘው የሠራተኞች ኮንፍዴሬሽን ሕንፃ ምድር ላይ የሚገኘው የጉምሩክ ሥነ–ሥርዓት ገቢ ሂሳብ ክፍል የጨረታውን ሰነድ ለመውሰድ የሚፈልግ ተጫራች የማይመለስ አንድ መቶ (100 ብር) በመክፈል ከላይ ከተጠቀሰው ቢሮ በአካል ቀርቦ መውሰድ ይችላል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን 5 ሺ በሊ/ፒ/ኦ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች ሰነዶችን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተረጋገጠ የድርጅቱ ማህተም በማድረግና በለም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/በተገኙበት ይከፈታል፡፡
የመንግሥት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ ወደተጠቀሰው የመ/ ቤቱ አድራሻ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 047-211 3452 ይደውሉ፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን የጅማ ቅ/ፅ/ቤት