የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር OR-UEAP/NCB/01/2013
1. በኢ/ኤ/አገልግሎት የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ኦሮሚያ ሪጅን ቢሮ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የመካከለኛ የጭነት ተሽከርካሪዎችን በመከራየት ለዲስትሪቢውሸን መስመር ዝርጋታ ስራ የሚያገለግሉ እቃዎችን፣ ምሰሶዎችን እና የቀን ሠራተኞችን የማጓጓዝ ሥራዎችን ለማከናወን የሚችሉ አይሱዙ ተሸከርካሪዎች ብዛት 4(አራት) በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዎችን ለአንድ ዓመት በኪራይ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ትራንስፖርተሮች መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት፤ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ያከናውኑበትን (ለ 2013 ዓም ማሰራት የሚችል ቦሎ) እና የተሸከርካሪዎቹን የኢንሹራንስ ዋስትና ማስረጃ (ሶስተኛ ወገን ለ2013 ዓም ማሰራት የሚችል) ከሚመለከተው ባለስልጣን (የመንግስት) መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፣
3 ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ማስታውቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) መከፈል መውሰድ ይችላሉ፣
4 አድራሻ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ፊት ለፊት በሚገኘው አማጋ ህንፃ 11ኛፎቅ፣
5 ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡
6 ተጫራች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር OR-UEAP/NCB/0/2013 የሚል ምልከት በማድረግ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት ድረስ እማጋ ሕንፃ 11ኛ ፎቅ በሚገኘው የሪጅኑ ቢሮ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባትይኖርባቸዋል፣
7 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ ባይገኙም ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓም በሪጅኑ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
8. የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5575209/5573898 መደወል ይችላሉ ::
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት
ፕሮግራም ኦሮሚያ ሪጅን ቢሮ