የተሽከርካሪ ኪራይ ጨረታ
የወጣ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ት/ክ/ኤ/አ/
001/2013 ዓ/ም
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ትግራይ ከልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፅ/ቤት ለሚያከናውናቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚውሉ ዳብል ጋቢና ፒክ አፕ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
ቀን |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
የሚፈለገው የተሽከርካሪ ብዛት |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
1 |
ደብል ጋቢና ፒክ አፕ |
6(እንደ አስፈላጊነት ስራው እየታየ (ሊጨምር ይችላል) |
ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት |
ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት |
- በጨረታው መስፈርቱን የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ ያላቸው የንግድ ድርጅቶች ወይም የተሽከርካሪ ባለንብረቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ ዓመታዊ የቴከኒክ ምርመራ ያከናወኑበትን እና የተሸከርካሪዎቹን 3ኛ ወገን የኢንሹራንስ ዋስትና ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ከዚህ በታች ከተጠቀሰው አድራሻ ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት ማግኘት ይቻላል፡፡ አድራሻ ፡– መቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ በሚገኘው የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 32፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጨረታው እንደሚያቀርቡት ተሽከርካሪ ብዛት ማለትም 1/አንድ/ ተሽከርካሪ የሚያቀርቡ ከሆነ 5,000.00/አምስት ሺህ ብር /2/ሁለት ተሽከርካሪዎችን የሚያቀርቡ ከሆነ 10,000.00/አስር ሺህ ብር/3/ሶስት ተሽከርካሪዎችን የሚያቀርቡ ከሆነ 15,000.00/አስራ አምስት ሺህ ብር እያለ በሚወዳደሩባቸው መኪና ብዛት ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በመስራቤታችን ስም ሲፒኦ /cpo/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማሰራት አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ት/ካ/ ኤ/አ/001/2013 ዓ/ም የሚል ምልክት በማድረግ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒ በመፃፍ እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትግራይ ክልል ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 31 ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ክልሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፅ/ቤት