የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡-
ኢንሥኮ ገማአዘ/ብግቤ 3/2013 ዓ.ም
የግዥ መለያ ቁጥር (ሎት) |
የግዥው አይነት |
ብዛት |
1 |
የእህል መቋጠሪያ የሚለጠፍ ታግ/ስቲከር |
500,000 |
በዚሁ መሰረት፡– በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፋ ለ2013 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባየምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰነዶች በቴከኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው :: ከጨረታ መክፈቻው ቀን በኋላ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150.00(አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ከጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 -6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡00 -10፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 -6፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ በመያዝ ብሎክ 1 ቢሮ ቁጥር 206 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ (አድራሻው ከስር ተገልጿል፡፡)
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ጥቅምት 27 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድና ቼከ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የቴከኒክ መወዳደሪያ ሰነዳቸውንና ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን በግልጽ ከፋፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1 (አንድ)
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርሰንት) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ግዥ፣ ንብረት አስተዳደር ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ቡድን አስተባባሪ
ደብረዘይት መንገድ ኢትዮ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ
ቅርጫፍ ፊት ለፊት
ፖሳ.ቁ. 7858
ስልክ ቁጥር 0411 4167345/011 4669336
Email. abdisida@gmail.com
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን