የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉባቦር ዞን የዲዱ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም የበጀት ዘመን በወረዳ ላሉት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽዳት ዕቃዎች
- ኤሌክትሮኒክስና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች)
- የደንብ ልብሶችና የስፌት ዋጋ
- የመኪና ጎማና የሞተር ሳይክል ጎማ
- ለቴክኒከና ሙያ ሥልጠና የሚያገለግሉ መሣሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
❖ በዚሁ መሠረት በጨረታው ሳይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የቲን ነምበር ያላቸውና የ2012 ዓ.ም የመንግሥት ግብር ከፍለው ያጠናቀቁና ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የሚቀርበው ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ(ኦርጅናል እና ኮፒ) ሆኖ ሠነዱ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቶች በመልካም ሥራ አፈፃፀም ወይም የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስተው ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የጨረታውን ሰነድ በኢሉባቦር ዞን ከዲዱ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ት/ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ በመቅረብ የአንዱ ሠነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ለጽሕፈት መሣሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽዳት ዕቃዎች በ7/1/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን በኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች (ፈርኒቸሮች)በ7/1/2013 ዓም ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሆኖ ተወካዮች ሕጋዊ የውክልና ደብዳቤና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡ለደንብ ልብሶች፣ለደንብ ልብስ ስፌት ዋጋ ለቴክኒከና ሙያ ሥልጠና የሚያገለግሉ መሣሪያዎች፣ የመኪና ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማ በ8/1/2013 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- የዕቃው ማስከበሪያ ቦታ የዲዱ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ሆኖ መገጣጠም ማስጫኛና ማውረጃ ትራንስፖርት ወጪ በአጠቃላይ የሻጭ ግዴታ ናቸው፡፡
- ክፍያ የሚደረገው የተጠየቁ ዕቃዎች ባጠቃላይ ገቢ ሲሆኑና እንደ ኤሌክትሮኒክስ ያሉ ዕቃዎች በባለሙያ ታይተው ተቀባይነት ሲያገኙ ብቻ ከፍያው ይደረጋል፡፡
- በሌላ ተጫራቶች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- የዕቃ ብዛት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
- የተጠየቀው ዕቃ በተጠየቀው ሰነድ መሠረት ሞልተው ማቅረብ እና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብ አለበት፣ ያልተጠየቀውን ዕቃ ቢሮ ካዘጋጀ ሰነድ ውጭ /በሌላ/ ካቀረበ እንዲሁም ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ከፋክቱር ጋር አዘጋጅተው ማቅረብ የሚችሉ (ዕቃዎቹና ፋክቱር) መለያየት የለበትም፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃዎች በተለይ የደንብ ልብስ እንዲመረጥ ዘንድ ማለትም ለናሙና የተለያዩ ከሦስት ዓይነት ያላነሰ ጨረታ ጨርቅ እንዲሁም ጫማ ከሦስት ያላነሱ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- በተራ ቁጥር 1-15 በተገለጸው መስፈርት ያልተስማማ በጨረታው ላይ መሳተፍ የለበትም፡፡
ለበለጠ መጃ በስልክ ቁጥር፡– 0113434573/0913377582
በኢሉባቡር ዞን የዲዱ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት