ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአ.ብ.ክ.መ በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ በኮን ከተማ የሚገኘዉ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ለኮሌጁ አገልግሎት የሚዉሉ
- ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃ
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃ
- ሎት 3 የደንብ ልብስ
- ሎት 4 የጋርመንት/የልብስ ስፌት የትም/ዕቃዎች ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ሥለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል ::
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፤
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚቸሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ነበር ያላቸዉ
- የግዡ መጠን ብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- የሚገዙ የዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒዉን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከህዳር 14/03/2013 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/03/2013 ዓ.ም ዘወትር በስራ ስአት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ/መግዛት/ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 29/03/2013 ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡3ዐ ላይ ይከፈታል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመልስ የእያንዳንዱ 50ብር / አምሳ ብር / በመክፈል በኮን ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል::
- የጨረታዉ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ማሻሻያ ማረግና እራሳቸዉን ከጨረታዉ ማግለል አይቻልም፤
- ዉድድሩ የሚካሄደዉ በሎት ድምር ዉጤት ነዉ::
- ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ መጠን 1/አንድ / በመቶ የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና በጥሪ ገንዘብ ማሰያዝ አለባቸዉ::
- ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ዉጭ መሆኑን መግለጽ አለባቸዉ::
- ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስም፣ ፊርማ፣ የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል::
- አሸነፊዉ በተጠቀሰዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት ንብረቱን ዕቃዉን ማቅረብ አለበት ከተጠቀሰዉ ስፔስፊኬሽን ዉጭ ይዞ ቢቀርብ በሚደረሰዉ ኪሳራ ተቋሙ ተጠያቂ አይሆንም:: ንብረቱ በባለሙያዉ ተፈትሾ ነዉ ገቢ የሚሆነዉን:: ጥራት የጎደለዉ ዕቃ ኮሌጁ ያለመረከብ መብት አለዉ::
- በማንኛዉም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይቻልም::
- ኮሌጁ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
- ተወዳዳሪዎች በጨረታዉ አሸናፊ የሆኑና ከተገለጸላቸዉ በአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- በጨረታዉ አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 5/አምስት /ተከታታይ ቀን ድረስ በኮሌጁ ቀርቦ ዉለታ መዉሰድ ይኖርበታል፤
- ኮሌጁ በሚገዛው ዕቃ ላይ እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ተጫራች የቫት የምስክር ወረቀት አብሮ ማስያዝ ይጠበቅበታል::
- ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ባዕል ቀን ከሆነ/ዝግ /ከሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይሆናል::
- ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0334430081 ወይም ዐ334430143 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
የኮን ከተማ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ