ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አፋር -01/2013
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ2013 መደበኛ እና ካፒታል በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትንለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ማለትም
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የኮምፒዩተር አክሰሰሪዎችን እና
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታአወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት
- በመንግሥት አቅራቢነት የተመዘገበ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ያለው
- ተጫራቾች በየሎቱ/በሚወዳደሩበት ዕቃዎች 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ይመለስላቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያበአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስና አቅም ግንባታ ቢሮ የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 32 የማይመለስ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ በሚያቀርበው የዕቃዎች ዋጋ በግልጽና በማያሻማ መልኩ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ከዚህ መመሪያጋር በተያያዘ ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የነጠላ እና የጠቅላላ ዋጋውን ከነቫቱ ሞልቶ ከላይ የተጠቀሱትና ማስረጃዎች አሟልቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሠመራ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስና አቅም ግንባታ ቢሮ ምድር ላይ በሚገኘው የመረጃ ዴስክ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ እና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚዘጋ ሆኖ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን