Computer and Accessories / Equipment and Accessories / Machinery and Equipment / Office Furniture

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና መንደር ማሰባሰብ ጽ/ቤት አገልገግሎት ላይ የሚውሉ ፈርኒቸር የእህል ወፍጮ እና የኤሌከትሮኒክስ እቃዎችን የአገር ውስጥ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ፡

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና መንደር ማሰባሰብ ጽ/ቤት አገልገግሎት ላይ የሚውሉ

 • ፈርኒቸር፣ የእህል ወፍጮ እና የኤሌከትሮኒከ ስእቃዎችን የአገር ውስጥ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ 

የተጫራቾች መመሪያ 

 1.  ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ ማወዳደሪያ መስፈረቶችን ማለትም፡ 1.1 የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ 1.2 ለሚቀርቡት እቃዎች የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው፣ 1.3 ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው፣ 1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ 1.5 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመእና 1.6 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው 
 2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናቶች በአፋር ብ/ክ/መንግስት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና መንደር ማሰባሰብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 3.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲፒኦ(CPO) ወይም ባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ / ኮንትራክት ቦንድ/ ካስያዙና ውል ከተፈራረሙ በኋላ ለጨረታ ማስከበያ ያስያዙት /Bid bond/ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች ለየብቻ በማሸግና አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለእያንዳንዱ በማድረግ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሚያቀርቡት እቃ የሚሸጡበትን ዋጋ ቫትን አስገብተው በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እንዲሁም የተጫራቾችን ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም በማኖር ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ 
 5. የጨረታውቆይታ ጊዜ፡- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ለ10 የስራ ቀናቶች የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን በስራ ሰዓት እንዲሆን ተጠብቆ 11፡00 ሰአት ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በማግስቱ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት በአፋር ብክ/መንግስት የተቀናጀ የተፋሰስልማትና መንደር ማሰባሰብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ 
 6. ተጫራቶች ለመጫረት የሚፈልጉትን እቃዎች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ መግለጽ እና ማመልከት አለባቸው ፡፡ 
 7. ተጫራቶች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸው ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡ 
 8. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን የእቃ ዝርዝር በመከተል ዋጋውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተመለከተው መስፈርት መሰረት መሙላት አለባቸው፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ 
 9. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ያቀረቡትን ዋጋ መለወጥ ወይም ከጨረታ ውድድር መውጣት አይች ሉም፡፡ ያልተሞሉ መረጃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 10. በዋጋ ማቅረቢያ ላይ የሚካተቱት ወይም የተጠቀሱት እቃዎች መስፈርቶቹ መስሪያቤቱ በሚፈልገው ዝርዝር መግለጫ (Specifica tion) ተሞልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 11. ማንኛውም ተጫራች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ 
 12. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ለምንያህል ቀናት ጸንቶ እንደሚቆይ በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
 13. ጽ/ቤት ተጫራቾቹ ላሸነፉባቸው እቃዎች ዋጋ የሚከፍለው ካሸናፊ ድርጅት ጋር በሚያደርገው ህጋዊ የሽያጭ ውል መሰረት ይሆናል ፡፡ ከፍያው በኢትዮጵያ ብር ይሆናል፡፡ 
 14. ተጫራቾች ለመጫረት የሚፈልጉትን እቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ የለባቸውም፡፡ 
 15. ማንኛውም ተጫራቶች ያለበቂ ምክንያት የተዋዋለውን ውል ካፈረሰ ለስራው አፈጻጸም ዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በመቀጫ ስም ለጽ/ቤት ገቢ ይሆናል፡፡
 16. ገዥው መስሪያ ቤት ለአሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ማሸነፉ በጽሁፍከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ከ 5 ቀናት በኋላ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡
 17. መስሪያ ቤቱ ገዥው ለእያንዳንዱ እቃ ያቀረበውን ዋጋ ሳይለውጥ የሚገዛውን እቃ ብዛት 25% ለመቀነስ ወይም ለመጨመር ይችላል፡፡ 
 18. አሸናፊ ድርጅት እቃዎችን የሚያስረክብበት ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሲሆን እቃዎቹን የሚያስረክብበት ቦታ ደግሞ ሠመራ በሚገኘው የአ/ብ/ክ/መ/የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና መንደር ማሰባሰብ ጽ/ቤት መጋዘን ይሆናል፡፡ 
 19. ገዥው መስሪያ ቤት ጨረታው ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በፊት ከተጫራቾች ሊሻሻል የሚገባው ሀሳብ ከቀረበለት እና አሳማኝ ሆኖ ካገኘው የጨረታ ሰነዱን ሊያሻሽለው ይችላል። ለተጫራቾች ማሻሻያ ሀሳቦች ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት በጽሁፍ ያሳውቃል፡፡ 
 20. አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በተጠቀሰው ጊዜ የማስረከብ ወይም የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ 
 21. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም የጨረታ ውድድር ጥያቄን መ ቤቱ አይቀበልም፡፡ 
 22. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ሁሉ ተጨማሪ ማብራሪያ በአ ብ/ክ/መ/የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና መንደር ማሰባሰቢያ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመገኘት መጠየቅ ወይም በቢሮው ስልክ ቁጥር 033666828 ወይም 0911810981 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
 23. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 24. ቅድሚያ ማወዳደሪያዎቹን ሙሉ በሙሉ ያለፉ ተጫራች አሸናፊውን ለመለየት የእቃው ዋጋ ዝርዝር መግለጫ ለግምገማ የሚያገለግሉ መስፈርቶች ይሆናሉ፡፡ 

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና መንደር ማሰባሰብ ጽ/ቤት