በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዳማ ዞን የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በተለያዩ አካባቢዎች በUHDP በካፒታል ኢንቬስትሜት እቅድ ውስጥ በUHDP CW-017/2019 /2020 ተብሎ የተያዘው ከአፖስቶ ድልድይ እስከ ፖሊስ ኮሌጅ ( Aposto Bridge to police college) ሊዘረጋ የተያዘው የመንገድ ዳር መብራት (steel pole street light installation Project ) ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
- በፌደራል ወይም በክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በአቅራቢነት በዘርፉ የተመዘገቡ።
- በኤሌክትሮ ሜካኒካል ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾች።
- የቫት ተመዝግቢ የሆኑ።
- የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) 100,000 ( አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማሳዣ ወይም CPO ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ህጋዊ ፍቃዳቸውን ተእታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክመንት ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ 15 ተከታታ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከይ/ዓለም ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍለው የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ከይ/አለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሴክተር መውሰድ ይቻላል።
- የጨረታ ሰነድ ለየአንዳዱ የጨረታ ሰነድ አይነት አንድ አርጅናልና ሶስት ኮፒ ለየብቻቸው በሰም ታሸጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ከቶና በሁሉም ዶክሜንት ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት እዲሁም አድራሻ በመጻፍ ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ከይ/አለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ ሴክተር ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጅው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- አሰሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ያስገባው ዋጋ አርትሜትክ ቼክ ተሰርቶ ከሚገኘው ውጤት 2% ከፍ ካለ ወይም ዝቅ ካለ ተቀባይነት የለውም።
- ሪቨት ከ10% በላይ ማድረግ አይቻልም ::
የይ/ዓለም ከተማ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት