1ኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፤ –አ/ከ/ክ/ከ/ወ/5/ፋ/ጽ/001/13
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡–
- ሎት 1. የቢሮ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 4 የሠራተኞች ደንብ ልብስና ስፌት (የተሰፉ ሳምፕል ማቅረብ የሚችል)፤
- ሎት 5 የቢሮ መስተንግዶ፣
- ሎት 6. የመኪናና የሞተር ሳይክል ጥገና፤
- ሎት 7 የተለያዩ ጥገናዎች፣
- ሎት 8 የትራንስፖርትና የጭነት አገልግሎት
- ሎት 9 የህትመት ስራዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡:
በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የንግድ ምዝገባ፤ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና በፌደራል ግዥ ንብረት አስተዳደር ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር የጨረታ ሰነድ ስታስገቡ ለተወዳደራችሁበት አላቂ ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ፡፡ነገር ግን ከጠቅላላ ዋጋ ከ2% በታች ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ በየሎቱ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል በወረዳ 5 ፋ/ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስ/ዋና የስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን አካተው ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ በወረዳው ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፋችሁበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ለውል ማስከበሪያ 10% በCPO (በጥሬ ገንዘብ)ማስያዝ የምትችሉ፡፡ ነገር ግን የጨረታ ማስከበሪያ ለውል ማስከበሪያ ማድረግ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስገቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀን እና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡አጭር ጊዜ መስጠት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ከመድሓኒዓለም ት/ቤት በጤናው ሕንፃ ገባ ብሎ አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ ግቢ የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሕንፃ ውስጥ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡–ስልክ ቁጥር 011-2-73-26-68/011-2-73-75-80/
ማሳሰቢያ፡
- በተጫረታችሁበት ዕቃ ላይ ዋጋ ስታስገቡ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል
- መወዳደር የሚቻለው ንግድ ፍቃዱ ላይ በተሰጠው ስራ ዘርፍ ብቻ ነው
- ያስገባችሁት ሳንፕል ዕቃዎች ላሸናፊው ከተገለጸ በኋላ ባሉት 60 የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይኖርባችኋል፡፡ ካልወሰዳችሁ ግን ለሚፈጠረው ክፍተት ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት