የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2013 ዓ.ም የቢሮ – አላቂ ዕቃ : ደንብ ልብስ ፣ የጽዳት ዕቃ እና የመኪና ጎማ አወዳድሮ በግልጽ ማጫረት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 2. ልዩ ልዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 3. ደንብ ልብስ
- ሎት4. የመኪና ጎማ
በዚሁ መሰረት ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና TIN እና VAT ተመዝጋቢ የሆኑና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች የሚሞሉት የዋጋ ማቅረቢያ በጥንቃቄበፖስታበማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በሚያቀርቡት የሃሳብ መስጫ ላይ ስማቸውን፤ ፈርማቸውን ፤ አድራሻቸውንና የንግድ ድርጅታቸውን ማህተም ማኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ / ማድረግ አይችሉም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን አልፎ በቀጣዩ የስራ ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከአ/ከ/ክ/ከ/ወ7 ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታ በተዘጋ ዕለት 4፡30 ሰዓት ጨረታው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ይከፈታል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 3000 ሎት 2 4000 ሎት 3 2000 ሎት4 1000 በባንክ ከተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ከጨረታው መክፈቻ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር / በመክፈል ፋይናንስ ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ::
- ጨረታውን ተወዳድሮ ያሸነፈ ድርጅት አንዴ ውሉ ባይፈፅም ህጋዊ የሆነ እርምጃ በመውሰድ ውሉን የማቋረጥ መብት አለው
- ማናቸውም የጨረታ ህግ ያልተከተሉ አሰራሮች ከጨረታ ይሰረዛል፡፡
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን፣ ጊዜና ሰዓት ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት አለባቸው::
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩበት ዝርዝር ዕቃዎች መሠረት ናሙናውን አስቀድመው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ እና ከቫት ውጭ ያለውን ዋጋ መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን መጨመርና ስለመጨመሩን በግልፅ በፅሑፍ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች የዕቃውን መግለጫ (ዓይነት በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
ለተጨማሪም ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡– 0112732513 ደውለው ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ ::
ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ በመመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
አድራሻ፡–አውቶብስ ተራ ከፍ ብሎ ገነሜ ት/ቤት ፊት ለፊት
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
ወረዳ 7 አስተዳደር
ፋይናንስ ጽ/ቤት