ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2013
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
- ሎት 1 ስቴሽነሪ ዕቃዎች፣
- ሎት2. የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ ና የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት3. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሎት4. ህትመት፣
- ሎት 5 ፈርኒቸር፣
- ሎት 6. የፅዳት ዕቃዎች፣
- ሎት7. የላብራቶሪ ዕቃዎች፣
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታው ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቹ በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ 50 (ሀምሳ ብር በመከፈል) ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቀስተ ደመና የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁ 18 (ረዳት ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን። ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ከሎት 1-7 የሚሰላ ብር 2% በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ( CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአይራጃኛው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራጅ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት በሮ ቁጥር19 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበት የዉረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒው ለየብቻው በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚያበቃው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ታሽጎ ወዲያውኑ በዕለቱ 4፡00 ላይ በት/ቤቱ ግዢ ክፍል በቢሮ ቁጥር 19 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተግኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አካል የውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ሶስት (3) ቀን ስፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች መወዳደር አይችሉም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን ዕቃበራሳቸው ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ኵቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡- መሳለሚያ ወረዳን ከሞቢል ከፍ ብሎ እንገኛለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 2 1350 68 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና የመጀመሪያ
ደረጃ ት/ቤት