የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 5 የሚገኘው አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ ለ2013 ዓ/ም ሁለተኛ ዙር በጀት ዓመት የሚያስፈልጉትን እቃዎች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውንም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የ2013ዓ.ም በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው::
- የዘመኑ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት / የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከ100, 000 /አንድ መቶ ሺ በላይ ከተጫረቱት እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመከፈል የጨረታውን ሰነድ በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ግዥ ከፍል መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫት በመጨመር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ኮፒ በሰም በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 409 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በተለያዩ ጥፋቶች ያልታገዱ ።
- ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችል ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ እንደሚከተለው ይሆናል
ተ.ቁ |
የሎቶች ዝርዝር |
የግዥ አይነት |
CPO(ብር) |
1 |
ሎት 1 |
ደንብ ልብስ |
2000 |
2 |
ሎት2 |
አላቂ የቢሮ እቃና የጽህፈት መሳርያ |
3000 |
3 |
ሎት3 |
ህትመት |
2500 |
4 |
ሎት4 |
የህክምና መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች |
6000 |
5 |
ሎት5 |
የጽዳት ዕቃ |
3500 |
6 |
ሎት6 |
ኤለክትሮኒከስ እና የቢሮ እቃዎች |
2000 |
7 |
ሎት7 |
መስተንግዶ |
500 |
8 |
ሎት8 |
ቋሚ እቃ |
4000 |
9 |
ሎት9 |
የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ |
2500 |
10 |
ሎት10 |
የኮምፒዩተር እና የተለያዩ የእቃ ጥገና |
1000 |
11 |
ሎት11 |
የልብስ ስፌት |
2000 |
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አበበ ቢቂላ ጤና ጣቢያ ስም በተዘጋጀ በባንክ የተዘጋጀ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እያንዳንዱ እቃ የጥራት ደረጃና አስተማማኝነት የእያንዳንዱን ናሙና ጨረታው
- ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ለውድድር አናቀርብም፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠረው የስራ ቀናት በአስራአንደኛው ቀን ከቀኑ 10 00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቶች የወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የበተገኙበት በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡ አበበ ቢቂሳ ጤና ጣቢያ :- ከግሩም ሆስፒታል 300 ሜትር በኮብልስቶን ገባ ብሎ
ስተጨማሪ መረጃ ፡ስልክ ቁጥር 0112-7378 47
በአዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአበበ ቢቂሳ ጤና ጣቢያ