የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር AAWSA/WSIDD/NCB/GOV/NCS002/2020
በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን በ2013 እና 2014 በጀት ዓመት ከሚያከናውናቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ ስልጠናዎች ፤ ወርክሾፖችን፣ስብሰባዎችን ወዘተ የሚያዘጋጁ ሲሆን፤ ለዚሁ የሚሆን የምግብ፤ የትኩስ ነገርና ለስላሳ መጠጥ አቅርቦትና የአዳራሽ አገልግሎት የሚሰጡ፡
- ምድብ አንድ ፡– በምስራቅ አዲስ አበባ የሚገኙ ደረጃቸው ሦስት ኮኮብ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሆቴሎችን፤
- ምድብ ሁለት– ደቡብ አዲስ አበባ የሚገኙ ደረጃቸው ሦስት ኮኮብ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሆቴሎችን አወዳድሮ ቢያንስ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ከላይ የተገለጹትን የአገልግሎት አቅርቦት ውል መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ ሆቴሎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የህዝብ መናፈሻ ጎን የጋራ መኖሪያ ቤቶች መሃል ዲቪዥን መስሪያ ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር በመክፈል) መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ታክስ ክሊራንስ፣ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ሰርትፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ገዝርዝር የቴክኒክ ሰነድ እና የፋይናንስ በአንድ ኤንቬሎፕ ውሰጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንኩ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ከዋናው ሰነድ ጋር በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈበት የጠቅላላ ዋጋውን 10% (የውል ማስከበሪያ) ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ ለ60 (ስልሳ) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ጨረታው ህዳር 9/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከቀኑ በ8፡30 5ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይንት የለውም፡፡
- አንድ ተጫራች በሁለቱም ምድብ መሳተፍ የሚችል ሲሆን፤ ነገር ግን በሁለቱም አቅጣጫዎች (ምስራቅ እና ደቡብ አዲስ አበባ) ሆቴሎች ሊኖሩት ይገባል፡፡
- ተጫራቾች ዲቪዥን መ/ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል። የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት። ይህንን ያልገለጸ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- ዲቪዥን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን አድራሻ፡– ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ-08 ፣ የቦታው ልዩ ስም፡– ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡– +251 11 8291312 (1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል)
በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ