የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2012 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን የመርካቶ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት
- ንቃይ ሙሉ ቆርቆሮ፣
- የብረት በር ባለ ሁለት ተካፋች፣
- የመስታዎት መስኮት፣
- የእንጨት ሸልፍ፣
- የጀኔሬተር ቤት መለስተኛ፣
- የብረት በር ባለ አንድ ተካፋች፣
- ጀኔሬተር ባለ 12 ኪሎ ዋት ፒስተን ሄድ የጎደለው የሌለው የፈነዳ፣
- የፕላሲቲከ ወንበር የተሰባበረ፣
- ኦሎፒያ ካልኩሌተር አዲስ፣
- ሌዘር ቦርሳ ያገለገለ፣
- ስቴፕለር መምቻ መካከለኛ፣
- ስቴፕለር መምቻ ትንሹ፣
- የወረቀት መብሻ ትንሹ 520፣
- የወረቀት መብሻ ካንጋሮ 720 መካከለኛ፣
- የወረቀት መብሻ ትልቁ፣
- ጃይንት ስቴፕለር መምቻ፣
- በአይጥ የተበላ የቆሻሻ ቅርጫት፣
- ሴራሚክ 40 በ40፣ ዋይት ቦርድ፣
- ፕሮቶኮል መዝገብ፣
- የእጅ ባትሪ ትልቁ እና ትንሹ፣
- ዩፒኤስ 1000 ዋት፣ ውሃ ማጣሪያ፣ ሂተር፣
- የቲን አሻራ ቻርጀር፣
- የቲን አሻራ ማሽን ካሜራ፣
- የሴት ጫማ፣
- ጅንስ ሱሪ የወንድ፣
- የሹራብ ጃኬት የወንድ፣
- ጃኬት የወንድ፣
- የልብስ መኪና ሲንጀር አዲስ /chida TA-2/፣
- የሱፍ ካፖርት፣
- ተሽከርካሪ ወንበር፣
- የእንግዳ ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ባሉበት ሁኔታ የሚወገዱ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሰነዱን ገዝቶ መውሰድና የሚወገዱ እቃዎች ላይ በጨረታ በመግዛት መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናትና ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰባተኛ አማኑኤል ታክሲ መያዣ ጋር/ ወደ አማኑኤል ሲሄዱ በቀኝ በኩል የመጀመሪያው ቅያስ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን መርካቶ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት ለእያንዳንዱ ሎት (መደብ) ለተቀመጠው የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት” (ADDIS ABABA CITY GOVERNAMENT REVENUES AUTHORITY MERKATO No.2 M/T/P/BRANCH OFFICE) ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 15ኛው የስራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት ቀናት እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በ15ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋላይ ተንተርሶ ዋጋማቅረብ አይችልም፡፡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡በስልክ ቁጥር 011 276 89 62/011 273 27 71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች
ባለሥልጣን የመርካቶ ቁጥር 2
ቅርንጫፍ ጽ/ቤት