የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር፡ 001/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተሉትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት አንድ– የደንብ ልብስ /ደረጃውን የጠበቀ ሙሉ ሱፍ፣40% ሱፍ እና 60% ፖሊስተር ከሆነ ማቴሪያል የተሰራ ጨርቅ (ለኮትና ሱሪ፣ ለኮትና ጉርድ ቀሚስ ወዘተ የሚውል)
- ሎት ሁለት– የጽሕፈት መሣሪያዎችና እና የቋሚ አላቂ ቢሮ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት ሶስት – የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት አራት – የህትመት ውጤቶች (የተለያየ ቅጾችና ባነሮች-.ወዘተ)
- ሎት አምስት የአይቲ ዕቃዎች (server, licenced antivirus ,network cable…etc)፤ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ዲጂታል የውሀ ማጣሪያ ፣ቫኪዩም ክሊነር.ወዘተ) ፤ ለካፌ አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (የቡና እና ሻይ ማፍያ ማሽን ፣ፍሪጅ፣ኦቨን.ወዘተ)
- ሎት ስድስት – የቢሮ ፈርኒቸር
- ሎት ሰባት ለህጻናት ማቆያ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች (አልጋ፣ፍራሽ፣ መደርደሪያ፣ወንበር፣ አሻንጉሊቶች.ወዘተ)
- ሎት ስምንት – የተሸከርካሪ ጎማ፣ባትሪ እና የዳሽ ቦርድ ቅባቶች
- ሎት ዘጠኝ – የቢሮ ቁሳቁስ ግዥ/ የተለያዩ ቁልፎች —ወዘተ/
- ሎት አስር – የሆቴል አገልግሎት ግዥ (ከባለ ሁለት ኮኮብ እስከ ባለ አምስት ኮኮብ ደረጃ ያላቸው)
- ሎት አስራ አንድ – መጋረጃ ፣ ምንጣፍ እና ታይልስ
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ኘሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “ አንድ ኦርጅናል ኮፒ” የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎኘ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የስራ ቀን) ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 2% ፣ ለሎት ሁለት 2%፣ ለሎት ሶስት 2%፣ ለሎት አራት 2%፣ ለሎት አምስት 2% ፣ለሎት ስድስት 2%፣ ለሎት ሰባት 2%፣ ለሎት ስምንት 2%፣ ለሎት ዘጠኝ 2% ፣ለሎት አስር 10 ሺህ ብር ፣ ለሎት አስራ አንድ 2% በሚወዳደሩበት ሎት በባንክ በተመሰከረለት ቼክ CP0 ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው። CPO መስራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተእታ/ቫት/ ጨምሮ ወይም ተፈታ/ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለፁ ከሆነ ተእታ/ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው