የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍ/ቤት/01/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1– የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2- የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 3- የተለያዩ የደንብ ልብሶች
- ሎት 4 – የፎቶ ኮፒና የፕሪንተር ቀለሞች
- ሎት 5- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 6 –የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት 7- የህትመት ስራዎች
- ሎት 8- የሆቴል መስተንግዶ አቅርቦት
- ሎት 9- የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 10- የኮምፒውተር ፣ ፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ጥገና ስራዎች
- ሎት 11– የተለያዩ የቢሮ ጥገና እና ዕድሳት ስራዎች
- የግዥ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍርድ ቤት/01/2013
- ግዥው ግልጽ ጨረታ ነው
- ጨረታ ሰነድ የወጣበት ወር ህዳር 2013 ዓ/ም
ተጫራቾች ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፤ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የዋስትና ደብዳቤ የሚያቀርቡ ከሎት 9 እስከ 11 ለቀረቡት በሙያው የንግድ ፍቃድ ያላቸው ሆነው ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ሥራ ሰርተው የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው እና ላሸነፉበት ዕቃ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ እንዲሁም ቋሚ የስራ ቦታ ወይንም ድርጅት ያላቸው ሆነው በቅድመ ምልከታ ወቅት ድርጅታቸውን ወይንም የሥራ ቦታቸውን ለማሳየት ፍቃደኛ የሆኑ ከዚህ በፊት በፍርድ ቤቱ ጨረታ አሸንፈው በገቡት ውል መሰረት ግዴታቸውን የተወጡ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከግዥ ፈጻሚ የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ለተገለፁት ዕቃዎች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ድረስ ላሉት 1,000 ብር ሲሆን ከሎት 7 እስከ ሎት 11 ድረስ 500 መቶ ብር ወይም ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ያደራጃቸው መስሪያ ቤት ለዋስትናው ስፍርድ ቤቱ አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በየሎቱ በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመፃፍ እና የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከ 1 ቀን በፊት ለሚጫረቱበት በሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች በጨረታው ለመወዳደር ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ እና ድምር ዋጋ VAT ጨምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል። ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ ፍርድ ቤቱ ባስቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ወይም በሚቀርበው ናሙና ጥራት፤ ዋስትና ፤ አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል፡፡
- ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በየሎቱ የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው፡፡
- ኮፒ እና ኦሪጅናል ኤንቨሎፕ በተናጠል (ለየብቻ) በፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንጻ አጠገብ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 1ኛ ፎቅላይ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ
ቤት ቢሮ ቁጥር 17
ስልክ ቁጥር 0118-69-78-28/ 011-515-70-40
አዲስ አበባ ከተማስተዳደር የአዲስ
አበባ ከተማ ፍርድ ቤት