ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በስሩ የሚገኙትን ያገለገሉ ንብረቶች
- ምድብ አንድ ያገለገሉ ፈርኒቸሮችና ተያያዥ እቃዎች፣
- ምድብ ሁለት ያገለገሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡
1ኛ– ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሣር ቤት አካባቢ አፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዮቴክ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ግዥ፣ ንብረትና ጠቅ /አገ/ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
2ኛ– ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለምድብ አንድ 3000.00 (ሦስት ሺህ ብር) ለምድብ ሁለት 500.00 (አምስት መቶ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ብቻ በማስያዝ እስከ ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3ኛ– ጨረታው እስከ ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓም 4፡00 ድረስ አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታውም በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
4ኛ–ተጫርተው አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን እቃ ካወቁበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ ቀን ድረስ ያሸነፉበትን ዋጋ ለቢሮው በመክፈል ደረሰኙን በማሳየት እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት ማንሳት ይሆርበታል፡፡
5ኛ– ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ በመያዝ በቢሮው እቃ ማከማቻ (መገናኛ ደራርቱ ህንፃ ጀርባ) ንብረቶቹን በሳምንት ሁለት ቀን ሰኞ እና ሐሙስ ከጧቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ፡፡
6ኛ– ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡አፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት ዮቴክ ህንጻ 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01
ግዥ፣ ንብረትና በቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት
ስልክ. ቁ 0115575952
አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ