Audio Visual / Computer and Accessories / Construction Machinery and Equipment / Development and Web Design / Equipment and Accessories / Hand Tools and Workshop Equipment / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Photography and Filming Service and Equipment / Software Provision

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ት/ም ሥልጠና ቢሮ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2012 በጀት አመትቪዲዮ ካሜራ ፣ የደንብ ልብስ ፣ የኮንስትራክሽን ማሰልጠኛ ግብአቶች ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የሆቴል ሶፍትዌር ፣የፎቶ ኮፒና ፕሪንተር ቀለም ፣ ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

 

የጨረታ ማስታወቂያ 

የግዢ መለያ ቁጥር 02/2012 ዓ.ም 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ት/ም ሥልጠና ቢሮ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2012 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሎት ቁጥር

የግዥው አይነት ዝርዝር/ሎት

የጨረታ በማስከበሪያ መያዣ CP0

1

ቪዲዮ ካሜራ

10,000.00

2

የደንብ ልብስ

1,000.00

3

የኮንስትራክሽን ማሰልጠኛ ግብአቶች

10,000.00

4

ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች

8,000.00

5

የሆቴል ሶፍትዌር

10,000.00

6

የፎቶኮፒና ፕሪንተር ቀለም

10,000.00

7

ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር

20,000.00

ማሳሰቢያ 

 • ስለሆነምተጫራቶች በዘርፉ የተመዘገቡበትን፣ የታደሰ የንግድፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃዎችና በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ /ዌብሳይት/ ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢ/ያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
 • ከብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ በላይ ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
 • የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ /CPO/ ወይም የባንክ ጋራንቲ፣ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
 • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለጨረታ ሰነዱ መግዣ ለእያንዳንዱ ሎት የግዥ አይነት/ የተቀመጠውን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር ብቻ/ የኮሌጁ ክፍያና ሂሳብ ደጋፊ የሥራ ሂደት በመከፈል እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግዥ/ዕ/አፈፃፀም ቢሮ ቁጥር 009 መውሰድ ይቻላል፡፡
 • ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፖች/ፖስታዎች በማሸግ ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ምልክት /ፅሁፍ/ በማድረግ በአንድ ትልቅ ካኪ ፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
 • የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ፣ የባንክ ጋራንቲ ወይም ጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ፣ እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ካቋቋማቸው አካል የተሰጠ የዋስትና ደብዳቤ ኦርጅናል በታሸገው ፖስታ ውስጥ መካተት አለበት፡፡ በኦርጅናልና በቅጂው መካከል ያለመጣጣም ቢከሰት ኦርጅናል የበላይነት ይኖረዋል፡፡
 • በመጫረቻ ሰነዱ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡ ግምገማው ከ60 ቀናት በላይ የሚወስድ ከሆነ ኮሌጁ እንደአስፈላጊነቱ ግምገማው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተጫራቾች ያቀረቡትን የመጫረቻ ዋጋ እንዲያራዝሙ የመጠየቅ መብት ያለው ሆኖ ለማራዘም ፈቃደኛ ያልሆነ ድርጅት ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
 • የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ከተገለጸው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 • ጨረታዎቹ በተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
 • ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመርኩዞ መጫረት አይችልም፡፡
 • ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር የስራ ቀናት/ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 
 • የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻው ቀን በበዓል ወይምቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 • ተጫራቶች ጨረታው ከመዘጋቱ ከሦስት ቀን በፊት ናሙና እንዲቀርቡ ተጠየቀባቸው ናሙናቸውን በኮሌጁ ናሙና ክፍል ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ- ሥርአት አያስተጓጉልም፡፡
 • ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ማስታወሻ 

 1. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነዱ አንድ አካል ተደርጐ ይቆጠራል፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የሰፈሩት ዝርዝር መረጃዎች፣ በተጫራቾች መመሪያ እና ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በትኩረት ማንበብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ላይ ቫትን ካላካተቱ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል፡፡
 • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቅሬታ መስሚያ ቀናት ቅሬታ ካሉት በጽ/ቤቱ ማቅረብ ይቻላል፡፡ እንዲሁም ከ5 የቅሬታው መስሚያ ቀናት በኋላ ባለ 5 የስራ ቀናት ውል መውሰድ የሚችል፡፡
 • ለተጨማሪ ማብራሪያ ስቁ ፡- 0118 28 29 52
 • አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ት/ም ሥልጠና ቢሮ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 6 ኪሎ ከመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ት/ም 

ሥልጠና ቢሮ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ