የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002C/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግንባታ ስራዎች ስራዎችን የሚሰሩ የተለያየ ደረጃ ያላቸውን ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፦
ተጫራቾች ለሥራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው ፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝርየተመዘገቡ ፤ ወቅታዊ ታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ አጭር ምዝገባ ያደረጉና የ2013 ዓ.ም ያሳደሱ ተጫራቶች መሆን ይኖርባቸዋል።
- ሎት 1 ቂርቆስ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ (GC 5/BC 4 እና በላይ)
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 የስራ ቀናት ድረስ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በሰም በማሸግ የጨረታ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት 22ኛው የስራ ቀን ድረስ ባለው ጊዜ እስከ 4፡ 00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን (Technical & Financial Proposal ) ለእያንዳንዱ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የቅድመ ብቃት ጨረታ ሰነድ (Technical Proposal) በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራከሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 801 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት በባንክ ከፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች ከኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር ፕሮጀከት ካለው በእጁ ያሉት ፕሮጀከቶች ፋይናንሽያል ደረጃው ከ75% መብለጡን የሚገልጽ ማስረጃ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፡– የጨረታ መከፈቻው 22ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ