በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአግሮስቶን ምርትና ግንባታ ቴክኖሎጂ ማዕከል ብትን የሠራተኞች የደንብ ልብስ በሚቀርበው ልኬት መሠረት ሠፍቶ ማቅረብ (የመስፈያ ዋጋ ብቻ) ይፈልጋል

Tender
< Back

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአግሮስቶን ምርትና ግንባታ ቴክኖሎጂ ማዕከል ብትን የሠራተኞች የደንብ ልብስ በሚቀርበው ልኬት መሠረት ሠፍቶ ማቅረብ (የመስፈያ ዋጋ ብቻ) ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አግሮ 06/2012

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአግሮስቶን ምርትና ግንባታ ቴክኖሎጂ ማዕከል ብትን የሠራተኞች የደንብ ልብስ በሚቀርበው ልኬት መሠረት ሠፍቶ ማቅረብ (የመስፈያ ዋጋ ብቻ)

  1. ጨረታውን መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ በኢትዮጵያ የግብር ህጎች በተደነገገው መሠረት የዘመኑን የግብር ግዴታ መወጣትን የሚያመለክቱ ሰነዶች፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዌብ ሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማረጋገጫ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አግሮስቶን ምርትና የግንባታ ቴክኖሎጂ ማዕከል የሚል በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፣
  3. የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ፖስታ (Envelop) በማድረግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  4. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  5. በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልፆ በሚሰጠው የሥራ ትዕዛዝ መሠረት ውል ገብቶ ወደ ሥራ መሠማራት ይጠበቅበታል፣
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50/ሃምሣ ብር/በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
  7. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ቃሊቲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት CCRDA /ቤት ጎን ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡በስልክ ቁጥር 0114396001/0114394658 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት

ኮርፖሬሽን የአግሮስቶን ምርትና ግንባታ ቴክኖሎጂ ማዕከል