የጨረታው ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 1 ራዕይ ጤና ጣቢያ በ2013 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ
- የተለያዩ አላቂ የሕክምና እቃዎች ፣
- የደንብ ልብስ ፣ የደንብ ልብስ ስፌት ፣
- ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የተለያዩ የቋሚ እቃዎች ፣
- የጽዳት እቃዎች፣ የተለያዩ ህትመቶች እና መድሃኒቶች አወዳድሮ መግዛት ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታመሱ ህጋዊ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- ንግድ ፍቃድ ያደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቶች ቫት ተመዝጋቢና አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተጫራቶች የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 4ተኛ ፎቅ ቢቁ 408 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በሙግዛት መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በሁለት ፖስታ የሚወዳደሩበትን አይነት በፖስታው ላይ በመለየት ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጥዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ራዕይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 408 በመገኘት በዚህ የተዘጋጀው የተጫራቾች ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ራዕይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 408 በኮሚቴዎች ይከፈታል።
- እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት እና ሙሉ ሰነዱን ሳይገነጠል መመለስ አለበት።
- መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ በመስሪያ ቤቱ ስም 4000.00 [አራት ሺህ ብር/ ማሰራት አለባቸው፡፡ ነገር ግን የባንክ ክሬዲት ሌተር አንቀበልም::
- ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተካተተውን መረጃ በሙሉ ሞልተው መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለደንብ ልብስ ስፌት የሚወዳደሩ ተጫራቶች በሙሉ የደንብ ልብሱን በጨረታ አውጪው መ/ቤት ማሽን አምጥተው የሚሰፉ መሆን አለባቸው፡፡
- የቋሚ እቃ ተጫራቾች በፎቶ የተደገፈ ሣምፕል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- . ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟላ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከርና ጨረታውን ለማሳሳትና ለማጭበርበር የሚሞክር ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል፡፡
- . ተጫራቾች ለእያንዳንዱ እቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟሉ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከርና ጨረታን ለማጭበርበር የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
አድራሻ:- የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ራዕይ ጤና ጣቢያ ስልክ ቁጥር ፡- 011 8 93 25 88/011 8 93 22 55/011 8 93 29 88
በአዲሱ የካራ መንገድ ከአቅም ግንባታ ጀርባ እና ወሰን ግሮስሪ 200 ሜትር ገባ ብሎ፡፡
በየካ/ክ/ከተማ የወረዳ 11ራዕይ ጤና ጣቢያ