Building Construction / Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Finishig Works / Garments and Uniforms / Health Related Services and Materials / House and Building / Laboratory Equipment and Chemicals / Medical Equipment and Supplies / Others / Stationery / Textile

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 13 የኮልፌ ጤና ጣቢያ በ2013 በጀት አመት የመድኃኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት እንዲሁም የህክምና መገልገያ ዕቃዎች፣ የጤና ጣቢያውን ምድረ ግቢ በቴራዞን ጥገና ማድረግ ፣ የሰራተኞችን ደንብ ልብስ፣ ኣላቂ የቢሮ እቃ፣ የፅዳት እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የመለያ ቁጥር ኮ/ጤ/ጣ02/997/2013

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 13 የኮልፌ ጤና ጣቢያ በ2013 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች የተገለፁትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 • በሎት 1፡-የመድኃኒት እና የላቦራቶሪ ሪኤጀንት እንዲሁም የህክምና መገልገያ ዕቃዎች፣
 • በሎት 2፡- የጤና ጣቢያውን ምድረ ግቢ በቴራዞን ጥገና ማድረግ፣
 • በሎት 3፡- የሰራተኞችን ደንብ ልብስ፣
 • በሎት 4፡-ኣላቂ የቢሮ ዕቃ፣
 • በሎት 5፡- የጽዳት ዕቃ ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ መግዛትና ማስራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ::

የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ በባንክ የተረጋገጠ CPO 2% ማስያዝ አለባቸው።

 1. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበትን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጠውን የታደሰ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡ በሎት2 ላይ የምትጫረቱ ተጫራቾች ከግንባታ እና ኮንስትራክሽን ፍቃዳቸው ከደረጃ ስምንት እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል
 2. ተጫራቾች በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በመንግስት ስራ ሰዓት ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 13 ስር የሚገኘው በኮልፌ ጤና ጣቢያው ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 13 በአካል በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
 3. የጨረታ ዋጋ የሚሞላው ከጤና ጣቢያው በገዙት ሰነድ ላይ ሲሆን የሚወዳደሩበትን ዘርፍ ሁለንም መረጃዎች በሚገባ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡ አስቸጋሪ ሁኔታ ካጋጠመ የቀድሞ ቁጥር ሊነበብ በሚችልበት ሁኔታ በአንድ ሰረዝ ብቻ በመሰረዝ መሙላት ይችላሉ :
 4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የኣቅርቦት ዘርፍ ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን VAT ጨምሮ መሆን አለበት።
 5. ተጫራቾች ያቀረቡት ዕቃ ቢያንስ የአንድ አመት ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
 6. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉንና የሌሎች ማስረጃዎችን ለብቻው በአንድ ፖስታ ፣ሲፒኦ ደረሰኝ በአንድ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ኮፒ በአንድ ፖስታ በማድረግ በሚገባ በማሸግ በጀርባቸው ላይ ኦርጅናል ፣ኮፒ ፤ሲፒኦ በሚል መፃፍና እንደገና ሁሉንም ለብቻቸው የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሚገባ በፖስታው ጀርባ ላይ ኦርጅናል፣ኮፒ፣ ሲፒኦ ስሚል መግለፅ አለባቸው።
 7. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ ስሞሉበት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ እና በየደረጃው በታሸጉት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ ፊርማና ሥም እንዲሁም ህጋዊ ክብ ማህተም ማሳረፍ አለበት፡፡
 8. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 በተዘረዘረው መሰረት የሞሉትን እና ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ (አስራ አንድ ) የስራ ቀናት በመንግስት የስራ ስዓት እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው በጤና ጣቢያው ፋይናንስና ግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 በተቀመጠው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
 9. የጨረታው መክፈቻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ11(አስራ አንደኛ ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡
 10. በተጫራች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ60 (ለስልሳ) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
 11. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት የማጭበርበር (የሙስና) ተግባር ሲፈፅሙ ቢገኙ ወይም ለመፈፀም ቢሞከሩ በኢትዮጵያ ህጎች በተደነገገው ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
 12. ተጫራቾች የጨረታውን ሂደት ለማዛባት ቢሞከሩ ያልያዙት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ተወርሶ ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡በቀጣይም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
 13. ሳምፕል አቀራረብን በተመለከተ 5(አምስቱም) ሎት መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው እስፔሲፊኬሽን እና ሳምፕል ብቻ ተጫራቾች መወዳደር ይኖርባቸዋል ስለሆነም በየሎቱ የተዘጋጀውን እስፔሲፊኬሽን እንዲሁም ሳምፐሎች ሁሉም ተጫራች ማየት እና የተዘጋጀውን መውሰድ አለባቸው።
 14. ተጫራቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ተጫራች እስኪታወቅና ውጤት እስኪለጠፍ ድረስ ተመላሽ እይሆንም፡፡
 15. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ)በባንክ ማዘር CPO ወይም የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
 16. ውል ሲፈፀም ሆነ ከተፈፀመ በኋላ በጨረታው ሰነዱ ላይ ከሞሉት ዋጋ ውጪ ምንም ዓይነት ማስተካከያ ማድረግ አይቻልም፡፡
 17. አሸናፊ ተጫራቾች ከፍያ የሚፈፀምላቸው እንዲያቀርቡ የታዘዙትን ዕቃ በታዘዙበት ጊዜ በራሳቸው ወጪ በጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል በማቅረብ ሙሉ በሙሉ ሲያስረክብ እና የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሲያቀርብ ነው ::
 18. በግዥ አፈፃፀም በደል ደርሶብኛል የሚል ተጫራች ለአቤቱታው መሰረት የሆነውን የመጨረሻ ውሳኔ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ 5/አምስት የስራ ቀናት ውስጥ እቤቱታውን ጨረታ ላወጣው የመንግስት መ/ቤት የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የበላይ ኃላፊው መልስ ካልሰጠ ወይም በሚሰጠው መልስ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ ውሳኔው መስጠት ከነበረበት ጊዜ ገደብ ማብቂያ ቀን ጀምሮ 5/አምስት /የስራ ቀን ጊዜ ውስጥ ኣቤቱታውን ለአጣሪ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል ከዚህ ጊዜ በኃላ ለእጣሪው ኮሚቴ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም፡፡
 19. መሥሪያ ቤቱ ከተጫራቹ ጋር ከገባ የግዥ ውል አቅርቦት መጠን ላይ በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20%(ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
 20. በሎት 2 ላይ ተጫርታችሁ ያሸነፋችሁ ተጫራቾች 20%አድቫንስ ፔይመንት መስሪያ ቤቱ ሲለቅ ተጫራቹ በምላሹ 206 በቼክ አልያም በጥሬ ገንዘብ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
 21. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
 22. ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 -273-88-55/011280-10-21 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
 23. በጥቃቅን የተደራጁ ኣካላት ከሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ፣ በጽ/ቤቱ ስም፣ የጨረታ ቁጥሩንና ከላይ በቁጥር ከ1-5 በተገለፀው መሰረት የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን እይነት የሚገልፅ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

ለበለጠ መረጃ

አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ኮልፌ ጤና ጣቢያ

ኮልፌ አጠና ተራ ከፖሊስ ጣቢያው ከፍ ብሎ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የኮልፌ ጤና ጣቢያ