የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001sc/2012
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮንስትራክሽን ቢሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የክትትል፤ቁጥጥር እና ዲዛይን ማስተካከያ (Design Review) ስራዎችን የሚሰሩ አማካሪዎች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ለሥራው ህጋዊ ፍቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀትያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ፣ ወቅታዊ ታከስ ከሊራንስ የሚያቀርቡና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ቢሮ አጭር ምዝገባ ያደረጉና የ2012 ያሳደሱ የአማካሪ ድርጅቶች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ሎት 1 ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት እድሳት ስራ(CAE 5 እና ከዚያ በላይ)
- ሎት 2 ቂርቆስ ወረዳ 2 አስተዳደር ህንፃ ስራ (CAE 2 እና ከዚያ በላይ)
- ሎት 3 ቀጨኔ መድሃኒያለም ሴቶች እና ህፃናት (CAE 3 እና ከዚያ በላይ)
- ሎት 4 ን/ስ/ላ/ቴ/ሙያ ኮሌጅ ስራ (CAE 3 እና ከዚያ በላይ)
- ሎት 5 አዲስ ብድር እና ቁጠባ ቢሮ ህንፃ ስራ (CAE 2 እና ከዚያ በላይ)
- ሎት 6 3ቢ+ጂ15 ጤና ቢሮ ዋና ህንፃ ግንባታ ስራ (CAE1)
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ10 ቀናት ድረስ የማይመለስ 200.00(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በሰም በማሸግ የጨረታ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት 11ኛው ቀን ድረስ ባለው ጊዜ እስከ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን (Technical & Financial Proposal) ለእያንዳንዱ አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የቅድመ ብቃት ጨረታ ሰነድ (Technical Proposal) በዚህ ዕለት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 801ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሠረት በባንክ ክፍያ ትዕዛዝ / CPO/ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይቻልም፡፡
ማንኛውም ተጫራች ከአዲስ አበባ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በእጁ ፕሮጀከት ካለው በእጁ ያሉት ፕሮጀክቶች ፋይናንሻያል ደረጃው ከ 75% መብለጡን የሚገልፅ ማረጋገጫ ማስረጃ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– የጨረታ መክፈቻው 11 ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሠዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ