የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ለ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የጨ/መ/ቁ005/2012 ዓ.ም. ለሚያስገነባው ክሊኒክ የሚሆን የተለያየ የህክምና እቃዎችን አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፦
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከጤና ጥበቃ ከጤና ተቋማት/መረጃ ማቅረብ የሚችል
- የዘመኑን ግብር ከፍለው ፍቃድ ያደሱ
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይነት መለያ
- ቁጥር ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ በአቅራቢነት የተመዘገቡ የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር 10/ የስራ ቀናት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በቢሮ ሂሳብና ክፍያ ደጋፊ የስራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 04 በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፣፣
- ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ቫት VAT/ ማካተት አለባቸው ቫት ሳይካተት የቀረበ ዋጋ አለማካተቱን ካልተገለጸ እንዳካተተ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይኖርባቸውም፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ ሲፒኦ /CPO/ 15,000.00 /አስራ አምስት ሺ ህ ብር/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የሚጫረቱበት የመወዳደሪያ ዋጋ ሞልተው ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።ኛው ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ማሳሰቢያ፦ ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- አምስት ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ የድሮው ስፖርት ኮሚሽን ጊቢ ባለው ህንፃ ላይ 1ኛ ፎቅ አዲስ አበባ
- ሴ/ህ/ጉ/ቢሮ ለበለጠ መረጃ 0913719599 እና 0911802772
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ