ግልጽ ያጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቦል/ክ/ከ/ወ/15/ ፋ-02/2012
በአዲስ አበባ አስተዳደር ቦሌ/ክ/ከተማ ወ/15/ፋ/ጽ/ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አውጥቶ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡ –
- ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 የደንብ ልብስ ብር 5,000 ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ ብር 10,000 ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ብር 5,000 ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 10,000 ሎት 5 ፈርኒቸር ብር 5000 , 6. የደንብ ልብስ ስፌት ብር 1000 ሎት 7ፈርኒቸር ጥገና 1000 ሎት 8 ኤሌከትሮኒክስ ጥገና ብር 1000 ሎት 9 , ትራንስፖርት ብር 2,000 ሎት 10 ሕትመት ብር 2000 ሎት 11.መስተንግዶ ብር1000 በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ፣ ጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ወይም የባንክ ዋስትና ፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ ሰነዱን የማይመለስ ለየእያንዳንዱ ሎት ብር 50/ሀምሳ ብር/ ሀያት አደባባይ ዙሪያሽ ሞል 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቁ 504 ግዥ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ (Financial documents) ዋናና ቅጅ (original and copy) እያንዳንዱ ሎት ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ በወረዳው ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 504 G -5 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በወጣ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በወረዳው ግዥ ቡድን በአካል ቀርበው ውል መግባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በወረዳው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡
- በጨረታ ተሳታፊ የሆኑ ድርጅቶች የሚወዳደሩበትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ 3ቀን ቀድመው ለጽ/ቤቱ ማቅረብ አለባቸው :: አማራጭ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ ሃያት አደባባይ ወደ ጎሮ መስመር 500 ሜትር ገባ ብሎ ዙሪያሽ ሞል ላይ እንገኛለን፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች፡– 011 8931909/ 091405 84 79 ግዥ ቡድን ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ አስተዳደር ቦሌ
ክ/ከተማ/ወ/15/ፋ/ጽ/ቤት