የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዊ ብሔ/አስ/ዞን በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ የአገው ግምጃ ቤት ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2013 በጀት ዓመት ለአንደኛ ዙር ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ ለድርጅት ቤት መስሪያ የሚውል ቦታ ብዛት 14 እና ለመካዝን ቤት መስሪያ የሚውል ቦታ ብዛት 2 በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል:: በመሆኑ፡-
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላል::
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ብቻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 2 ማስገባት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተጫረተበትን የቦታ ስፋት በቦታው መነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከአምስት በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋና ሂሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል::
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ የሚመለሰው የጨረታ አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል::
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ይሆናል::
- ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀናት በ3፡00 ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዬቹም ሆነ ግለሰቡ ባይገኙ ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የሚከፈትበት ቦታ አገው ግ/ቤት ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ይሆናል::
- ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሰራ ቀናት ይሆናል::
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በማዘ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ 058 224 00 08/058 224 05 39 እና 058 224 05 34 ደውለው መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
- ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦችን ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይቻላል::
- ማዘጋጃ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የአገው ግምጃ ቤት ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት