ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ለዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ
- የጽህፈት መሣሪያዎችን፣
- የጽዳት ዕቃዎችን፣
- የደንብ ልብሶችን እና
- ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሳተም ይፈልጋል:: ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች
የተጠቀሱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
- ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የዳንግላ ሆስፒታል ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት መወዳደር የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 72 ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ዳንግላ ሆስፒታል ግዥ ፋይ/ ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 72 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይቻላል:: የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፊይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 72 በ16ኛው ቀን በ4፡30 ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎችን ዳንግላ ሆስፒታል ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ ንብርት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፣
- አሸናፊው የሚለየው በሎት /በጠቅላላ ዋጋ/ ወይም በነጠላ ዋጋ ሊሆን ይችላል፣
- . መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ቢሮ ቁጥር 72 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 81 40 05 74 ማግኘት ይችላሉ::
የዳንግላ ሆስፒታል