Land Lease & Real Estate

በአብክመ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሰንበቴ ከተማ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋታቸው 1636.03 ካሬ ሜትር የሆኑ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል

የመጀመሪያ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ ከሀ እስከ በተዘረዘረው መሰረት በሰንበቴ ከተማ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋታቸው 1636.03 ካሬ ሜትር የሆኑ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች፡

 1. የጨረታውን ሰነድ በሰንበቴ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማት ባንክ ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 3. ጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን (መለያ) መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
 4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5 (አምስት) በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒአ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም 5 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ከውድድሩ ይሰረዛል፡፡
 5.  ተጫራቹ የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦሮሞ /ዞን በሰንበቴ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን 8/10/2012 እስከ 19/10/2012 . ከቀኑ 1100 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን 19/10/2012 . በ11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
 7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 22/10/2012 . 400 ሰዓት ሰንበቴ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ (አዳራሽ) ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 8. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 1100 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በሰንበቴ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ስሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
 9. የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በሰንበቴ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
 10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-033 118 0376 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰንበቴ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት