ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን የአምባሰል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለ26ቱ ሴከተር መ/ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች
- ሎት1 የጽ/መሳሪያዎችን፣
- ሎት2 የፅዳት እቃዎችን፣
- ሎት3 የቢሮ ፈርኒቸር የሀገር ውስጥ፣
- ሎት4 የቢሮ ፈርኒቸር የውጭ፣
- ሎት5 የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎችን፣
- ሎት6 ቋሚ እቃዎችን፣
- ሎት7 የቴሌኮሚኒኬሽንና ተዛማጅ ዕቃዎችን፣
- ሎት8 የተዘጋጁ ልብሶች፣
- ሎት9 ብትን ጨርቅ፣
- ለት10 የህንጻ መሳሪያ
- ሎት11 የእንስሳት የህክምና ዕቃዎችን፣
- ሎት12 የመኪና ጎማ፣
- ሎት13 የውሃ ማከሚያ ኪካል፣
- ሎት14 የውሃ መገጣጠሚያ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ስለዚህ ጨረታውን መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ:
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያለው
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ በጨረታው የሚሳተፍ ሆኖ የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅበታል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00 /ሰላሣ ብር/ በመከፈል ከአም/ወ/ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ:
- የሚገዙ እቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ በጽ/ቤቱ እስከ 6/02/2013 ዓ/ም ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ የሚችል፣ በጥሬ-ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ጥሬ ገንዘቡን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይጠብቅበዎታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፐ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየትና በማሽን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6/02/2013 ዓ.ም የስራ ቀናት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርብዎታል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም/ በተራ ቁጥር 7 በተጠቀሰው ቀን በ6/2/2013 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን በሚያቀርብበት ወቅት ተሞከሮ (ቴስት) መደረግ የሚገባውን እቃ ተሞከሮ ለማስገባት ፍቃደኛ የሆነ
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች ማንኛውንም ወጭ ሸፍነው አምባሰል ወረዳ በእየ ፑል ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ወድድሩ ስሎት ድምር ወይም በነጠላ ሊሆን ስለሚችል በጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ ያሉ እቃዎች በሙሉ መሟላት አለባቸው፤ የጨረታ ሰነዱ ሙሉ በሙሉ ካልተሞላ እና ስርዝ ድልዝ፣በፍለድ ከተጠቀሙ ከውድድር ውጭ ይሆናል ፡
- ተወዳዳሪዎች የሚሞሉት ዋጋ የወቅቱን ገበያ ዋጋ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት ፣
- ተጫራቶች ጨረታውን ካሸነፉ ያሸነፉበትን ዕቃ ሣምፕል (ናሙና ) ማቅረብ የሚችል፣
- ጽ/ቤቱ በግዥ ጊዜ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች መጨመርም ሆነ መቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከአምባሰል ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ተገኝተው ወይም
- በስልክ ቁጥር /033224 0283/ 033224 02 14/ 033 224 0284 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአ.ብ.ክ.መ. በደቡብ በወሎ መስተዳድር ዞን
የአምባሰል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት