ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001/2012
በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት አመት ለግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት፡–
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 የመኪና ጎማ
- ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ
- ሎት 4 የሰራተኞች የተዘጋጁ የስራ ልብሶች
- ሎት 5 የሰራተኞች የስራ ጫማ
- ሎት 6 ቲትርን በግልጽ ጨረታ በሎቲንግ ሲስተም አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡
- የ2012/2013 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና ምዝገባ፣ ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነና መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ(ማስገባት) አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር /በመክፈል ግ/ወ/ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት ቢ ቁ 20 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በዝርዝር በተገለጸው እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ግ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት መግዛት ይችላሉ ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚወዳደሩበት እቃ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲፒኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ በመቁረጥ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ አሽጎ (አያይዞ) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታዎች በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰአት ይከፈታል ፡፡ የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ ከ5ኛው ቀን በኋላ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ስማስያዝ ከግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ ለማስረከብ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ የሚገዙት እቃዎች የማስረከቢያ ቦታ ግዳን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ስር ባሉ ንብረት ክፍሎች ውስጥ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ካስፈለገ በጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0332120008 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተጫራቾች መመሪያም ተያይዟል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
በአብክመ ሰ/ወሎ/ዞን የግዳን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ር ቡድን