በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣ ግልፅ የአካባቢ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመ/ማ/ም/ጠ/ፍ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የሚከተሉትን አቅርቦ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ እና ሌሎች አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2 ህትመት /ፋይል ፎልደር ሌቭል ቁጥር የስም ቲተር እና ማህተምን ይጨምራል
- ሎት 3 ደንብ ልብስ /ብትን ጨርቅ ጫማ እና የተዘጋጁ ልብሶችን/ የያዘ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ሎት 4 ላፕቶፕ /የኘላንት ማሽነሪ መሳሪያና ተዛማጅ እቃዎች /ላፕቶፕ እና ፕሪንተር/
- ሎት 5 ህንፃ ለቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች የቢሮ ጠረጴዛ እና ወንበሮች/
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የግዢው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ የፅህፈት መሳሪያ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 10 ብር በመክፈል በገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 0.5% ያሳነሰ ከ2% ያልበለጠ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ ሞልተው እንዲያቀርቡ አይገደዱም::
- የመጫረቻ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ማ/ም/ወ/ፍ/ቤት በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ12/02/2013 ዓ/ም እስከ 02/03/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በ02/03/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ይከፈታል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድና ቅዳሜ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወዲያውኑ ውል በመያዝ ንብረቶቹን ገዝቶ ንብረት ክፍል ማስገባት አለበት
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ፡-01162200148 /0921139915/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ
በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰሜን ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/ስ/ደ/የሥራ ሂደት