ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር መ/ግ /001/2013
ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቀበሌ 16 የሚገኘው የቢሮ መገልገያ ህንፃ አጠቃላይ ጥገና ስራ ለማሰራት ሲሆን በስልክ ቁጥር 0582209646/44 ፋክስ ቁጥር 0582220580 ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኜት ይቻላል፡፡የግንባታ ተጫራቾች BC 7 ; GC 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ በግንባታ ስራ አገልግሎት የተመዘገቡትን ለ2012 ዓ.ም የታደሰ የምስክር ወረቀት ህጋዊ ከሆነ አካል ማቅረብ የሚችሉ እና በግንባታ ሥራቸው የ2012 የመልካም ስራ አፈጻጸም ያላቸው
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
- የግዥ መጠን ብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በማቅረብ ለቢሮው ህንፃ አጠቃላይ ጥገና ለመስራት የሚያስችል የጉልበት የቁሣቁስና የመሣሪያ አቅርቦትን ያካተተ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶችን በታሸገ ፖስታ በማቅረብ በጨረታው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፣
- የህንፃ ጥገናውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣ ተጫራቾች የህንፃ ጥገናውን ጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ኘሮፖዛል ቅፆችን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 007 ማግኘት ይቻላል፣
- የህንፃ ጥገና ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ባሉ 180 መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት፣
- የሚያቀርቡት የህንፃ ጥገና የጨረታ ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ያካተተ የነፃ ገበያ ዋጋንና ወቅታዊ የቁሣቁሶችን ዋጋ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት ፣
- ተጫራቾች ለጥገና ስራው 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና የአሸነፈው ተጫራች በመቶ የመልካም ስራ ዋስትና አፈፃፀም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም የጥገና ስራ ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ 2 ቅጅዎች የዋጋ መሙያው ሰነድ ማለትም ዋናውና ቅጅው በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 007 የተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 21ኛ /ሀያ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባዋቸል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል በቢሮ ቁጥር 007 በ21ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በ9፡00 የሚከፈት ሆኖ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ መመሪያውን በጥብቅ በማንበብ መወዳደር አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 222 05 80 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582209646/44 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን