የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2012
በአብክመ ሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳት ሀብት ልማት ተ/ጽ/ቤት ለእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የስራ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃዎችን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ /የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ከነቫቱ መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ በማስላት ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ያስያዙበትንም ደረሰኝ ወይም CPO ዋናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የንግድ ፈቃድና የመሳሰሉት መረጃዎች ከኦሪጅናል ዶክሜንት ጋር ተያይዘው በፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
- በፖስታው በውጪ ገጽ እና በዋጋ መሙያው የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራች ስም፣ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል፤
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እንስሳት ሀብት ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 30.00 (ሰላሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ9/9/2012 እስከ 24/9/2012 ዓ.ም ለተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓላት ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ወይም በጥቅል መ/ቤቱ በሚያወጣው መሰረት ነው።
- የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋልዩነት ካለው የአንዱ ዋጋ የተሞላው ይወሰዳል፤ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ካለው ሰነዱን የሞላው ባለሙያ ፓራፍ ማድረግ አለበት፤ ይህ ካልሆነ ግን ሰነዱ ውድቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ በግዥ መመሪያው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- ተጫራቶች በጨረታ አፈጻጸም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጁ መሰረት በተከታታይ በየስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ለአሸናፊው ላቀረባቸው መድሃኒቶችና እቃዎች ዋጋ የሚከፈለው በውሉ መሰረት መድሃኒቶቹንና እቃዎቹን ከጽ/ቤታችን መድሃኒት ቤት ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ አጠናቅቆ ገቢ ማድረጉ ሲረጋገጥ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስ/ቁጥር 011685039/0052 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ
በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር
ወረዳ እን/ሀ/ል/ተ/ጽ/ቤት
መሀል ሜዳ፤