Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ቢ/ኮ አገልግሎት ጽ/ቤት ለሚሰራው የኮብል ስቶን መንገድ የመሬት ዝግጅት እና የጠጠር መንገድ ሥራ ለመስራት ያመች ዘንድ የማሽን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2013

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ቢ/ኮ አገልግሎት ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ በ3ቱም ቀበሌዎች ውስጥ ለሚሰራው የኮብል ስቶን መንገድ የመሬት ዝግጅት እና የጠጠር መንገድ ሥራ ለመስራት ያመች ዘንድ በማሽን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡

ስለሆነም:-

 1. በዘርፉ የወጣ ንግድ ፈቃድና በዘመኑ የታደሰ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ፣
 2. መለያ ቁጥር /ቲን/ ፣ ሊብሬ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የተመዘገባችሁበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የምትችሉ፣
 3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩት ማስረጃዎችን በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 4. የማሽን ኪራይ አቅርቦቱ የማሽኑ የማጓጓዣ ወጪ፣ የጥበቃ፣ ሥራውን ሲሰራ የሚጠቀመው ነዳጅ በማሽን አቅራቢው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
 5.  ለሥራው የሚያስፈልገው ሎደር እና ግሪደር ከ200 ሰዓት በላይ፣ ሮሎ ባለ 16 ቶን 120 ሰዓት በላይ እና ቼን ኤክስካቫተር ከ70 ሰዓት በላይ የሚፈጅ ሲሆን ሥራውን ሙሉ ለሙሉ በተፈለገው መጠንና ዓይነት ሰርቶ ለማስረከብ ሁሉንም ማሽኖች በወቅቱ የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል፣
 6. ተጫራቶች በቀረበው ዝርዝር መሠረት የምታቀርቡበትን ከጥቅል ዋጋው ላይ 1% CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በአጣ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ጽ/ቤት ግቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ፣
 7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150 ብር በመከፈል ከአጣ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የካላንደር ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30 ሰዓት ከአጣ ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛትና ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
 9. ጨረታ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዚህ ዕለት ከሰዓት በኋላ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
 10. ጨረታው በ16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 11. ተጫራቾች በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሞልተው ማቅረብ አይችሉም፡፡
 12. መ/ቤቱ ግዥውን በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
 13. በጨረታ አሸናፊው ተጫራች ለጽ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ዝርዝር ከጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል የመፈረም ግዴታ ያለበት መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
 14. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- 

 • መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 033 661 0688 ወይም በፋክስ 0336610234 ላይ ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
 • ጨረታውን የምናወዳድረው በጥቅል ስለሆነ በዝርዝሩ ውስጥ ላሉ የማሽን ዓይነት በሙሉ ዋጋ መሞሳትና ማቅረብ መቻል አለበት፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ያስጣዊ ከተማ አስተዳደር

ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት