የግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአቃ/ቃ/ክ/ከ የወረዳ 10 ለተለያዩ ለመ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፣
- ቋሚ፣ አላቂ፣
- የጽዳት ዕቃዎችና
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የደንብ ልብሶችን እና ሌሎች
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው በመሳተፍ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሥራው ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የ2012 ዓ.ም ግብር ከፍለው ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢዎች ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ 3000 (ሦስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነድ ወረዳ 10 ፋጽ/ቤት በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ በ10ኛውቀን ከ3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ሰነዱን መቀየር /ማሻሻል/ ከጨረታው ውስጥ መውጣት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ከየዓይነቱ አንዳንድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ የጨረታ ተወዳዳሪ ማሸነፉ ከተገለጸለት በኋላ በ3 ቀን ውስጥ ከግዢው ጠቅላላ ዋጋ 10 % የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በተመረጠው ናሙና መሰረት በራሳቸው ትራንስፖርት የተጠየቁትን ዕቃዎች አሟልተው በ3 ቀናት ውስጥ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ10 ፋ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አቅራቢው ተጫራች በውሉ መሰረት ግዴታውን ካልተወጣ ለውል ማስከበሪያ ያስያዙት10% ገንዘብና ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ሙሉ በሙሉ ውርስ ይሆናል፡፡
- ለሽያጭ ያቀረቡትን ዕቃዎች ጥራታቸውን ያልጠበቁ ከሆኑ አሸናፊው ተጫራች በራሱ ወጪ ዕቃውን የሚለውጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡
- የማስጫኛና ማውረጃ ወጪ በአሸናፊው ተጫራች ይሸፈናል፡፡
- ተወዳዳሪ ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው ጨረታው ከተፈጸመ በኋላ በ3 ቀን ውስጥ ወ /10ፋ/ቤት በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን በአ/ቃ/ ክ/ከተማ የወ/10ፋ/ጽ/ቤት ኮዬ ፈጬ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት 16 ጎን ለጎን ወደ ጎሮ መሄጃ በስተቀኝ በኩል አካባቢ
ስልክ ቁጥር፡– 0922246475/0912801867
በአቃ/ቃ/ክ/ከ ወረዳ10
አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት