የጨረታ ማስታወቂያ
ቁ-01/2013
በአርሲ ዞን የአሰኮ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤
- ፈርኒቸር፤
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤
- የመኪና ጎማዎች እና
- የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን (የማሽን አይነት ካት ዶዘር D8R 2013ና በላይ፣ ካት ግሬደር 2013ና በላይ፤ ካት/ዶሰን/ ሀይንዳይ እስካቫተር 2013ና በላይ፣ ሎደር 2013 ና በላይ፣ ሩሎ 2013 ና በላይ ና ሲኒዮ ትራክ) ከባለንብረትና ህጋዊ የሆነ የማሽነሪ አከራይ ፍቃድ ካላቸው አከራዮች ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየትና መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም:
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ያላቸው እና በፌደራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ወይም በግዢዎች ና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ)እንዲሁም ፤ ለጽዳት እቃዎች፤ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ) በጽ/ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000209216578 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ጉዳይ ቢሮ ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ክፍል ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለኤሌክትሮኒክስ እና ለመኪና ጎማዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) ፣ ለጽህፈት መሳሪያዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000.00 (ሰድስት ሺህ) ፤ ለፈርኒቸር እና ለጽዳት እቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ) እንዲሁም ፤ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ) ለኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ለእያንዳንዱ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ(CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።
- በማይክሮ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ማህበራት ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ከተገለጸው የጨረታ ሠነድ ማስከበሪያ የብር መጠን ጋር የሚመጣጠን የዋስትና ደብዳቤ ካደራጃቸው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሽናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹንና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰኮ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0221191003) (0912296366) (0920047605)(0922287801) ይጠይቁ።
በአርሲ ዞን የአሰኮ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/በት