Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Equipment and Accessories / Garments and Uniforms / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Spare Parts and Car Decoration Materials / Stationery / Textile

በአርሲ ዞን የሸርካ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች የጽዳት እቃዎች፣ ትናንሽ ቋሚ እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች)፤ የመኪና ጎማና የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2013 

በአርሲ ዞን የሸርካ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

 • የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች
 • የጽዳት እቃዎች፣ ትናንሽ ቋሚ እቃዎች፤
 • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች)፤
 • የመኪና ጎማና
 • የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡

 1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር ከፍለው፤ የንግድ ፈቃዳቸዉን ያሳደሱና በፌዴራል ወይም በክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበትን፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
 2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢዉ መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀዉ ለመክፈላቸዉ እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 3. ተጫራቾች ለጽህፈት መሣሪያዎች ፤ የፅዳት እቃዎች፤ ትናንሽ ቋሚ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የቢሮ ፈርኒቸሮች፤ የመኪና ጎማና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 30.00 (ሠላሳ) በሽርካ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎቤሳ ቅርንጫፍ በባንከ ኔትዎርከ በሂሳብ ቁጥር 520C22000006 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በጽ/ቤቱ የግር የንብረትና አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በመቅረብ ብሩን ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ /አድቫይስ ይዞ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች በኦርጅናልና በኮፒ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ካዘጋጁ በኋላ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት በመሙላት ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 6. የተጫራቾች ሙሉ ስም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱ ማህተምና አድራሻ የሌለው ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 7. የጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዞች ለዚህ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ እንደዋስትና የሚያገለግል ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ሥራዎች ጽቤት ብቻ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 8. . አሸናፊው ተጫራች የእቃዎቹ ናሙና ቀርቦ እንዲታይ ከተፈለገ የተፈለገውን ዕቃ ለማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
 9. . ተጫራቾች የእቃዎቹን ዋጋ ከዚህ ሠነድ ውጪ በሌላ ዋጋ መስጫ ላይ ሞልተው መመለስ አይችሉም፡፡ 
 10. ተጫራቾች የሃገሪቱን የፌዴራልና የክልሉን የግዥ አዋጆች፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን የማክበርና ከማንኛውም የሙስና ድርጊቶች ነፃ የሆኑ እንዲሁም፤ በእቃ አቅርቦት ወቅት ከዚህ ሰነድ ጋር የተያያዘውን የውል ሠነድ መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡ 
 11. አሸናፊ ተጫራቾች ለያንዳንዱ እቃ የሰጡት ነጠላ ዋጋ እስከ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም. ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው ጽ/ቤቱ ተጨማሪ የግዢ ጥያቄፍላጎት ባቀረበበት ወቅት ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸውና ውል መፈፀም የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል:: 
 12. አሸናፊ ተጫራች ጽ/ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት የሚችል መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 13. ተጫራቾች የሠራተኞች የደንብ ልብስ ዓይነቶችን (ብትን ጨርቅ፤ የተዘጋጀ ልብስና ጫማዎችን) ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 14. ማንኛውም ተጫራች የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፤ ትናንሽ ቋሚ እቃዎች ፤የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የቢሮ ፈርኒቸሮች፤የመኪና ጎማና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ወይም ሲፒኦ (CPO) በሽርካ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ስም በማሠራት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች ሲ.ፒ.ኦ (CPO)ውን ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 15. አሸናፊ ተጫራች ለዉል ማስከበሪያ ያስያዘዉ የገንዘብ መጠንእስከ ሦስት ወር የጊዜ ገደብ ድረስ ገቢ ያደረጋቸው ዕቃዎች ለተጠቃሚው መ/ቤት ደርሰው የብቃት ደረጃቸው ትክክለኛነት እስኪረጋገጥ ድረስ የማይመለስ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡ 
 16. ተጫራቶች በማንኛውም ሁኔታ የጨረታውን እካሄድ ሥነሥርዓት ለማስቀየርም ሆነ ለማሳሳት ከሞከሩ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ተደርጎ ወደፊት በሚወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ እንዳይሳተፉ ይደረጋል:: 
 17. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው የእቃ ዋጋዎች (የመወዳደሪያ ሃሳቦች) ተጨማሪ እሴት ታክስ ማካተቱንና አለማካተቱን በግልጽ መግለጽ ይኖርባቸዋል:: ይህ ያልተገለጸ ከሆነ የተሰጠው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳካተተ ይወሰዳል፡፡ 
 18. አሸናፊዉ ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነየዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ ወጪ በማጓጓዝ የታዘዘውን ዕቃ በአንድ ላይ ሽርካ ወረዳ ጎቤሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ 
 19. ጽ/ቤቱ ተጫራቾችን ሲያጫርት ለጨረታው ቅድመ ግምገማ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን የተጫራቾች መመሪያ መሠረት በማድረግ ለቀረቡት የዕቃ የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ የዕቃዎቹን ጥራትና ብቃት በማረጋገጥ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት አሸናፊ ይሆናል፡፡
 20. በጨረታው ማስታወቂያ ውስጥ ያልተገለጹ መመሪያዎች ካሉ ሥራ ላይ ባሉት የመንግሥት የግዥ አዋጆች፤ ደንቦችንና መመሪያዎች መሰረት የሚፈጸሙ ይሆናሉ፡፡ 
 21. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ጠዋት 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት በ5፡30 ሰዓት ጽ/ ቤቱ ውስጥ ለአመቺነቱ በተመረጠው ቦታ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡ 
 22.  ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: 

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-(022 446 0311) (022 446 0086) ይጠይቁ፡፡ 

በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት