የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 03/2012
በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር የመንግስት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በአስተዳደሩ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ከዚህ በታች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1/ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃ፣ ጋሪዎችና የደንብ ልብስ ስፌት ፣
- ሎት 2/ የኮምፒውተር የፕሪንተር ተዛማች እቃዎች
- ሎት 3/ ጠረጴዛ ፣ ወንበሮችን፣ ሼልፍ
- ሎት 4/ የመኪና ጎማዎች የመሳሰሉትን በጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡
- በመንግስት ግዥና ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱበት እንዲሁም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ሌተር ኦፍ ክሬዲት ሲፒኦ ባንክ የሚሰጣቸውን ማስረጃዎች እና በጥሬ ገንዘብ የሚያቀርቡትን ዋጋ ሎት 1/ 1000.00 አንድ ሺህ ብር ብቻ ሎት 2/ 5000.00/ አምስት ሺህ ብር ብቻ ሎት 3/ 3000.00 ሶስት ሺህ ብር ብቻ ሎት 4 /3000.00 ሶስት ሺህ ብር ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ታክስ የሚከፍሉበትን ክ/ከተማ ወረዳ በጨረታው መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ካላቀረቡ ከጨረታው በራሳቸው ጊዜ በፍቃዳቸው እንደወጡ ይቆጠራል
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን መስሪያ ቤቱ በሰጣቸው የአንድ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላትና የድርጅታችሁን ማህተም ፊርማ ሙሉ ስም ኣድራሻቸውን ስልክ ቁጥር በመግለጽ አንድ ኦርጅናል እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ቫት ያላካተተ የመወዳደሪያ ሰነድ ከጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር ብቻ / በመከፈል ሰነዱን ለመግዛት ይችላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉብትን ንብረት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ ወረዳ 09 ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዕቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በታሸገ ኤንቨሎፕ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ 302 በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ በዚሁ እለት በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– አራት ኪሎ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አለፍ ብሎ ሲፒዩ ኮሌጅ ፊት ለፌት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፤-0118684714 /0118951941/
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር