የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክ/ከተማ የአፄፋሲል የመዋዕለ ህጻናትና የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት በ2013 ዓ.ም የመጀመሪ ዙር ግልጽ ጨረታ ከመንግስት በተገኘ መደበኛ በጀትና ከውስጥ ገቢ
- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- የትምህርት እቃዎችና መጽሀፍቶች፣
- የስራ ልብስና ጫማዎች የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ የህክምና እቃዎች፣
- የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣
- ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና የሰራተኞች የስራ ልብስ ስፌት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር በአቅራቢነት የተመዘገበና በመንግስት እቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ::
- 2ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የሙያ ዘርፍህጋዊየታደሰንግድፍቃድያለው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡:
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ፡ ፋይናንስ ቢሮ መውሰድይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ት/ቤቱን ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላትና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰአት ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቤተመጽሀፍት ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ብር 2000(ሁለት ሺ ብር ) በት/ቤቱ ስም በተዘጋጀ ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ አለባቸው::
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊልየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የዋጋ ማቅረቢያ በተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከክፍል 4 ላይ በመመሪያው መሰረት ስለተያያዘ ሁሉም ተጫራች ዋጋ እዛ ላይ መሙላትአለበት፡፡
- አድራሻ፡ አጼ ፋሲል የመዋእለ ህጻናትና የመ/ደ/ት/ቤት ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወረድ ብሎ ይገኛል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡-011812-46-87 ይደውሉ፡፡
- ማሳሰቢያ፡- የስፌት ዋጋ ለምትጫረቱ ተጫራቾች ት/ቤቱ በሚያዘጋጀው ቦታየስፌት ማሽናችሁን ይዛችሁ በመምጣት ይሆናል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ በአራዳ
ክ/ከተማ ትም/ጽ/ቤት የአጼ ፋሲል መዋዕለ ህፃናትና የጀመሪያ ደረጃ የመንግስት ት/ቤት