የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክ/ከተማ የመልካም እርምጃችን የአፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን
- ሎት 1 የደንብ ልብስ ፣
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣
- ሎት 3 አላቂ የትምህርት እቃዎች ፣
- ሎት 4 የፅዳት እቃዎች ፣
- ሎት 5 የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት 6 ቋሚ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ላይ መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት እና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የስራ መስኩ በጀርባ ገፅ ይመልከቱ የሚለው በትክክል የሚገልፅ መሆን አለበት፡፡
- የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰሰም የታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመልካም እርምጃችን አፀ/ህፃ/የመ/ደ/ት ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የሚመለስ 5000 (አምስት ሺህ ብር) በመልካም እርምጃችን የአፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት ስም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር በፋይናንስ ቢሮ ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሎት 5 ደንብ ልብስ ስፌት ተወዳዳሪዎች ግን የሚመለስ 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በመልካም እርምጃችን የአፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት ስም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ስፔስፊኬሽን ያልወጣላቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ ለገዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን መሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፡– ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት አጠገብ
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡– 0111111012/+251111264656 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ የመልካም እርምጃችን
የአፀደ ህፃናትና ያመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት