የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በ ዚሁ መሰረት ተጫራቾች መስፈርቱን ማሟላት የምትችሉት፡
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2012 ዓ/ም፤
- ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን ቀለም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡
- 1ኛ በሙያው ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- 2ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለተጫረቱበት ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(cpo) የሚያቀርቡ፡፡
- 3ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- 4ኛ ሰነዱን ብር 100 የማይመለስ በመክፈል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በወረዳው ፋ/ፅ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይቻላል፡፡
- 5ኛ. ተጫራቾች ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የሚሸጡበት ዋጋ በተዘጋጀው ቅፅ ላይ በመሙላት የድርጅታችውን ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ ወረዳው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- 6ኛ የጨረታ ሳጥኑ በአስራ አንደኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 7ኛ ቫት ከፋይ የሆነ 8ኛ ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-ከጣይቱ ሆቴል ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 0118787323/0111112287/
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 1 የፋይናንስ ጽ/ቤት